የህይወት ወሳኝ ምዕራፎች ባንክ አግልግሎት

ኦቪድ ቤቶች ባንክ አ/ማ

በምሥረታ ላይ

ሰላም፤ እንተዋወቅ

የኦቪድ ቤቶች ባንክ አላማና የስራ እቅድ አብዛኛውን የሕብረተሰብ ክፍል አሳታፊ በሆነ መንገድ ሐብት አሰባስቦ፣ ይህን ሐብት መልሶ ደንበኞቹን፣ የአክስዮን ባለቤቶችንና፣ ሐገርን በሚጠቅም የፋይናንስ አገልግሎት ስራ ላይ ማዋል ነው

ኦቪድ የቤቶች ባንክ

ኦቪድ ቤቶች ባንክ ኣ/ማ በኢትዮጲያ ንግድ ህግ አንቀጽ 245፣ በባንክ ስራ አዋጅ ቁጥር 592/2000 እና የባንክ ስራ አዋጅን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 1159/2011 መሰረት እየተደራጀ ያለና በባንክ አገልግሎት ላይ የሚሰማራ የአክስዮን ማህበር ነው።

አዋጭ ነው

የኦቪድ ቤቶች ባንክ ለአክስዮን ባለቤቶች አትራፊ ክመሆን ባለፈ፤ በአገራችን የፋይናንስ አገልግሎትን ተደራሽና አካታች በማድረግ፣ የሐገራችንን ከፍተኛ የዜጎች የመኖሪያ ቤት ዕጦት ችግር ለመቅረፍ የበኩሉን ድርሻ በማበርከት፣ ለኢኮኖሚያችን ዕድገት አስተዋፆ የሚያበረክት መሆኑን አደራጅ ኮሚቴው ያምንበታል።

ቀድሞ መግዛት ብልህነት ነው

ስለሆነም የዚህን አትራፊና አዋጭ ባንክ አክሲዮን በመግዛት ባቀድናቸው በጎ ተግባራት መሠረት ክሚገኘው የትርፍ ጥቅም ተካፋይ እንዲሆኑ በታላቅ ትህትና እና አክብሮት እንጋብዛለን።

ኦቪድ ቤቶች ባንክን መመሥረት ለምን አስፈለገ?

እስኪ የሚከተሉትን ልብ እንበል

01

የኢኮኖሚ ዕድገት

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እያደገና ወደ ፊትም እድገቱ የሚቀጥል መሆኑን የተለያዩ ጥናቶችና መረጃዎች ያመለክታሉ። የኮንስትራክሽንና ግንባታ ስራ መስፋፋት፣ የአምራች ኢንዱስትሪ ፓርኮች መገንባትና ሥራ መጀመር፣ አንዲሁም የዉጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ማበረታቻዎች ለተመዘገበው የኢኮኖሚ ዕድገት ተጠቃሽ ምክንያቶች ናቸው። የሰዎችም ወደ ከተማ ፍልሰት ከዚሁ ጎን በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ነው።

02

እስካሁን ያለው የባንኮች ሚና

ባንኮች በዜ ሂደት ላይ የሚከተሉትን በጎ አስተዋፅኦች አድርገዋል።

  • የዜጎችን የቁጠባ ባህል ማሳደግ
  • ለገለሰቦችና ድርጅቶች የብድር አግልግሎት መስጠት
  • አለም አቀፍ ንግድን ማሣለጥ (ማበረታታት)
  • ለባላአክሲዮኖቻችው ተገቢ ትርፍ መክፈል
  • ለዜጎች የስራ እድል መፍጠር
  • ለመንግስት የግብር ገቢን በመጨመር

03

እንዲያም ሆኖ የቀጠለው የቤቶች ችግር

  • የቤቶች ፋይናንስ አገልግሎት ማግኘት አእቸጋሪ ነው።
  • ሲገኝም፣ አብዛኛውን አገልገሎት ፈላጊ አካታች አይደለም።
  • በቤቶች ግንባታ ሴክተር ዙሪያ ያለው የፋይናንስ ፍላጎትና አቅርቦት በጣም አይመጣጠንም።
  • በነዚሀና ሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች፣ የመኖሪያ ቤቶች እጥረት ችግር ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰ መጥቷል።
amAM