እንገናኝ

ብናገኝዎ እንወዳለን። ጥያቄዎችዎን ለመመለስና እስተያየትዎን ለማድመጥ ዝግጁ ነን።

ብዙ ጊዜ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

መግዛት የምችለው ዝቅተና የአክስዮን ብዛት ስንት ነው?

አንድ ግለሰብ ወይም ኩባንያ መግዛት የሚችለው ዝቅተኛ የአክስዮን ብዛት 200 አክሲዮኖች ነው። አክሲዮን ሲገዙ ለመግዛት የሚፈልጉትን የአክሲዮን ብዛት ዋጋ 25% (ክ 5% ተጭማሪ የአገልግሎት ክፍያ ጋር) መጀመሪያ ከፍለው፣ የቀረወን ገንዘብ ባንኩ ሥራ ክጀመረበት ቀን ባሉት ሁለት አመታት ውስጥ ከፍለው መጭርስ ይችላሉ። (ለምሳሌ የ 200 አክሲዮን ዋጋ 200,000 ሺ ብር ሲሆን፣ በመጀመሪያ 25% ውይም 50,000 ሺ ብር (አና 10,000 የአገልግሎት ክፍያ) ከፍለው ለአክሲዮኖቹ ግዢ የመዘገቡና የቀረውን 150,000 ባንኩ ሥራ ከጀመረበት ቀን በሁለት አምታት ውስጥ ይከፍላሉ ማለት ነው።

አንድ ግለሰብ ወይም ኩባንያ መግዛት የሚችለው ከፍተኛ የአክስዮን ብዛት ስንት ነው?

አንድ ግለሰብ ወይም ኩባንያ መግዛት የሚችለው ከፍተኛ የአክስዮን ብዛት 1,000,000 አክሲዮኖች ወይም በአጠቃላይ 1,000,000,000 ብር ዋጋ ያላቸው አክሲዮኖች ሲሆን፤ አክሲዮን ሲገዙ ለመግዛት የሚፈልጉትን የአክሲዮን ብዛት ዋጋ 25% (ክ 5% ተጭማሪ የአገልግሎት ክፍያ ጋር) መጀመሪያ ከፍለው፣ የቀረወን ገንዘብ ባንኩ ሥራ ክጀመረበት ቀን ባሉት ሁለት አመታት ውስጥ ከፍለው መጭርስ ይችላሉ።

ኦቪድ ቤቶች ባንክ መቼ ሥራ የጅመራል?

በመንግስት መመሪያ መሠረት፤ ኦቪድ ቤቶች ባንክ ለሽያጭ ካቀረባቸው ጠቅላላ አክሲዮኖች ውስጥ 25% ማለትም 5 ሚሊየን አክሲዮኖች (5 ቢሊየን ብር ዋጋ ያላቸው) ሸጦ ሲጨርስ ሥራ ይጀምራል።

አንድ የባንኩ ባለአክሲዮን ቤት ለመግዛት ወይም ለመስራት ብድር ቢፈልግ፣ ባንኩ ብድር በማመቻቸት ያግዘዋል?

አዎ፣ አንድ የባንኩ አክሲዮን ባለቤት ብድር ለማግኘት መሟላት ያለባቸውን ሕጋዊ መስፈርቶች ካሟላ፣ የጠየቀውን ብድር ለማምቻቸት ባንኩ ጥረት ያደርጋል።

አክሲዮን መሸጥ መቼ ትጀምራላቸው?

ኦቪድ ቤቶች ባንክ ጥር 14, 2016 የመጀመሪያውን የአክሲዮን ሽያጭ (IPO) ጀምሮአል። ይህ ፕሮግራም በተሳካ ሁኔታ መጀመሩን ስንነግራችሁ በደስታ ነው። የም ማለት፣ በ3 ሰዓት ውስጥ 1.2 ቢሊዮን ቢር የሚያወጡ አክሲዮኖች ለመሽጥ ችለናል። (ይህ ስኬት የአክስዮን ሽያጭ ፍጥነትና ብዛት ሲታይ ክንረወሠን ነው ብልን እንግምታልን)። በተጨማርም ፈጣን የአክሲዮን ግዢ፣ የገዙት ተቋማትና የግለ ባለሀብቶች በኦቪድ ቤቶች ባንክ ላይ ያሳዩት የእምነት ድምፅ ነውና እናመሰግናለን። የተሳካ ባንክ ለመመሥረት የምናረገውን አስደሳች ጉዞ ሳይረፍድ እንድትቀላቀሉም በአክብሮት እንጋብዛለን። ልብ ይበሉ፤ የየአክሲዮኖች ሽያጩ ሁሉም አክሲዮኖች ሲሸጡ ወይም አክሲዮን መሸጥ ክጀመረንበት ቀን 6 ወር ቀድሞ በተከሰተው ቀን ያቆማል። መጀመሪያ ቀን እንዳየነው ከሆነ፤ ሁሉም አክሲዮኖች ተሽጠው ላማለቅ ብዙ ጊዜ የሚፈጅ አይመስልም።

ቢሮአችሁ የት ነው?

እባክዎ ስለ አድራሻችን ዝርዝር (የቢሮአችንን ቦታ ጨምሮ) በድረ-ገፁ "እንገናኝ/Contac Us" ክፍል ውስጥ የቅርብ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ።

አክሲዮን ስለ መግዛት በበቂ መረጃ የተደገፈ ውሳኔ ለማድረግ ምን ሌላ መረጃ ያስፈልገኛል?

በኦቪድ ቤቶች ባንክ ስልቀረበው የአክሲዮን ሽያጭ የተሟላ መረጃ ለማግኘት እና በእውቀት ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ለማድረግ እባክዎን የኦቪድ ቤቶች ባንከን የአክሲኦን ሽያጭ መግላጫ (Prospectus) ያንብቡ።

ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ይውጪ ሐገር ዜጎች አክሲዮን መግዛት ይችላሉ?

አዎ ትችላለህ. ይሁን እንጂ ሽያጩ የሚካሄደው ለእንዲህ ዓይነቱ ሽያጭ በወጣው ደንብ መሠረት ነው ። ለምሳሌ የንግድ ልውውጦቹ በቢር ሳይሆን ተቀባይነት ባለው የውጭ ገንዘብ መካሄድ አለባቸው።

amAM