ኢንቬስተር ግንኙነት

ከጥር 14 / 2016 ጀምሮ አክሲዮን ለመሽጥ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ አግኝተናል።

ከመጀመሪያዎቹ የአክሲዮን ባለቤቶች መሀል እንዲሆኑ የኦቪድ ቤቶች ባንክ በታላቅ ክብር ይጋብዝዎታል።

20,000,000

ለሽያጭ የቀረቡ አጠቃላይ የአክሲዮኖች ብዛት

(20 ቢሊዮን ብር)

ይህም ሁሉንም የሚያካትት፣ በቀላሉ የሚገኝ፣ እና አትራፊ የሆነ ባንክ ለመፍጠር የገባነውን ቃል በተሻለ ሁኔታ ለመወጣት ያስችለናል።

200

አንድ ግለሰብ ወይም ድርጅት መግዛት የሚችለው ዝቅትኛው የአክሲዮን ብዛት

(ሁለት መቶ ሺ ብር ዋጋ ያለው)

ወደ ሰፊው የኅብረተሰባችን ክፍል የመድረስ ፍላጎታችንን የሚያሳይ ሌላው ምልክት ነው ።

1,000,000

አንድ ግለሰብ ወይም ድርጅት መግዛት የሚችለው ከፍተኛው የአክሲዮን ብዛት

(1 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያልው)

ይምጡ፣ ይጎብኙን። ኦቪድ ቤቶክ ባንክ ላይ ኢንቨስት ማድረግ (የሼር ባለቤት መሆን) በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ምርጥ ኢንቨስትመንቶች እንዴት አንዱ ሊሆን እንደሚችል እንወያይ።

5 billion Birr

ሥራ ለመጀመር በሕግ የተቀመጠው ዝቅተኛው የተከፈለ የካፒታል መጠን።

የአክሲዮኖቻችንን የአትራፊነት ዕድል ስንገምትና የአክሲዮን ሽያጭ ሒደቱን ፍጥነት ስናይ፣ የቀሩት ኢክሲዮኖች በሙሉ ተሽጠው በቅርቡ ሥራ እንጀምራለን ብለን እንጥብቃለን።

ስለዚህ አስደሳች አጋጣሚ ይበልጥ ለማወቅ መጥው እንድያነጋግሩን እናበረታታዎታለን

ስለ ኦቪድ ቤቶክ ባንክ አ/ማ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እባክዎን ከዚህ በታች ያለውን መግለጫ (Prospectus) አውርድው ያንብቡ።

በተጨማሪም እንደ ግለሰብ ወይም እንደ ኩባንያ አክሲዮን ለመግዛት የሚሞላውን የማመልከቻ ቅፆች ከዚህ በታች ማውረድ ይችላሉ።

አክሲዮን ለመግዛት ትክክለኛውን ቅፅ (ማለትም፣ የግለሰብ ወይም የኩባንያ ማመለካቻ ቅፅ) ከሞሉ በኋላ፣ አክሲዮናችንን በወኪልነት እየሸጡ ካሉት ባንኮች ውስጥ ወደሚመችዎ በመሄድ የሚፈልጉትን የአክሲዮን ብዛት ዋጋና የአገልግሎት ክፍያ ይፈጽሙ። የባንኮቹን ስም ዝርዝርና ትክክላኛ ሒሳብ ቁጥሮች (Account Nos.) ከዚህ በላይ ያለውን ፎርም ላይ ያገኛሉ።

ያስተውሉ፡ ሊገዙ ከሚፈልጓቸው ጠቅላላ የአክሲዮን ዋጋ ላይ 1/4 ኛውን (ወይም 25%) ብቻ በቅድሚያ በመክፈል አባል መሆን ይችላሉ። ቀሪውን ገንዘብ ባንኩ ሥራ ከሚጀመረበት ቀን ጀምሮ በሁለት ዓምት ውስጥ ከፍለው ማጠናቀቅ የችላሉ።

amAM